«ቶም እና ጄሪ» ፊልም
ዊልያም ሐና እና ዮሴፍ ባርባራ በተባሉ ባለሞያዎች ለሜትሮ ጎልድዊን ካምፓኒ የተሠራ ተከታታይ የካርቱን ፊልም
ነው፡፡ የቤት ውስጥ ድመት በሆነው በቶም እና በተንኮለኛዋ አይጥ በጄሪ መካከል በማያቋርጥ ቅንቃኔ እና ጠላትነት
እየተቀጣጠለ የሚሄደው ይሄ ፊልም፣ አስገራሚም አስቂኝም ነው፡፡
በ1940 እኤአ የተጀመረው ቶም እና ጄሪ፣የአኒሜሽኑ ኩባንያ እስከ ተዘጋበት እስከ 1957 እኤአ ብቻ 114 ያህል ተከታታይ ፊልሞችን በሐና እና በባርባራ ደራሲነት እና አዘጋጅነት አቅርቧል፡፡
በ1940 እኤአ የተጀመረው ቶም እና ጄሪ፣የአኒሜሽኑ ኩባንያ እስከ ተዘጋበት እስከ 1957 እኤአ ብቻ 114 ያህል ተከታታይ ፊልሞችን በሐና እና በባርባራ ደራሲነት እና አዘጋጅነት አቅርቧል፡፡
በ1960 እኤአ በአዲስ መልክ ፊልሙ እንደ ገና
መዘጋጀት እና መታየት ጀመረ፡፡ ዛሬ በታይም ዋርነር ካምፓኒ ባለቤትነት እና በዋርነር ብሮስ አከፋፋይነት የተያዘው
የቶም እና ጄሪ የካርቱን ፊልም 162 ተከታታይ ፊልሞችን ያጠቃልላል፡፡
ቶም እና ጄሪ አብረው በአንድ ሰው ቤት ውስጥ
የሚኖሩ ነገር ግን መቼም ቢሆን ተስማምተው የማያውቁ ፍጡራን ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ በጥቅም ምክንያት ሲስማሙ እንኳን
በአከፋፈሉ ምክንያት ለመጣላት ጊዜ አይወስድባቸውም፡፡ ሁለቱንም የሚቃረን ነገር ከመጣ ግንባር የሚፈጥሩት ቶም እና
ጄሪ፣ የጋራ ጠላታቸውን ለየራሳቸው ምክንያት ሲሉ ካጠቁ በኋላ እንደገና እርስ በርሳቸው መጣላት ይቀጥላሉ፡፡